1 Chronicles 6

ሌዊ

1የሌዊ ወንዶች ልጆች፤
ጌድሶን፣ ቀዓት፣ ሜራሪ።
2የቀዓት ወንዶች ልጆች፤
እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል።
3የእንበረም ልጆች፤
አሮን፣ ሙሴ፣ ማርያም።
የአሮን ወንዶች ልጆች፤
ናዳብ፣ አብዩድ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር።
4አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤
ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤
5አቢሱ ቡቂን ወለደ፤
ቡቂ ኦዚን ወለደ፤
6ኦዚ ዘራእያን ወለደ፤
ዘራእያ መራዮትን ወለደ፤
7መራዮት አማርያን ወለደ፤
አማርያ አኪጦብን ወለደ፤
8አኪጦብ ሳዶቅን ወለደ፤
9ሳዶቅ አኪማአስን ወለደ፤
አኪማአስ ዓዛርያስን ወለደ፤
ዓዛርያስ ዮሐናንን ወለደ፤
10ዮሐናን ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም ባሠራው ቤተ መቅደስ በክህነት ያገለገለ ነበር፤
11ዓዛርያስ አማርያን ወለደ፤
አማርያም አኪጦብን ወለደ፤
12አኪጦብ ሳዶቅን ወለደ፤
ሳዶቅ ሰሎምን ወለደ፤
13ሰሎም ኬልቅያስን ወለደ፤
ኬልቅያስ ዓዛርያስን ወለደ፤
14ዓዛርያስ ሠራያን ወለደ፤
ሠራያ ኢዮሴዴቅን ወለደ።
15 እግዚአብሔር የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በናቡከደነፆር እጅ ተማርከው እንዲወሰዱ ባደረገ ጊዜ ኢዮሴዴቅም አብሮ ተማርኮ ሄደ።

16የሌዊ ወንዶች ልጆች፤
ጌድሶን፣ ቀዓት፣ ሜራሪ።
17የጌድሶን ወንዶች ልጆች፤
ሎቤኒ፣ ሰሜኢ።
18የቀሃት ወንዶች ልጆች፤
እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል።
19የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤
ሞሖሊ፣ ሙሲ።

በየአባቶቻቸው ቤተ ሰብ የተቈጠሩት የሌዊ ጐሣዎች የሚከተሉት ናቸው፤
20ከጌርሶን፤
ልጁ ሎቤኒ፣ ልጁ ኢኤት፣
ልጁ ዛማት፣
21ልጁ ዮአክ፣
ልጁ አዶ፣ ልጁ ዛራ፣ ልጁ ያትራይ።
22የቀዓት ዘሮች፤
ልጁ አሚናዳብ፣ ልጁ ቆሬ፣
ልጁ አሴር፣
23ልጁ ሕልቃና፣
ልጁ አቢሳፍ፣ ልጁ አሴር፣
24ልጁ ኢኢት፣ ልጁ ኡርኤል፣
ልጁ ዖዝያ፣ ልጁ ሳውል።
25የሕልቃና ዘሮች፤
አማሢ፣ አኪሞት።
26ልጁ ሕልቃና፣
አንዳንድ የዕብራይስጥ ቅጆች፣ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕምና የሱርስቱ ቅጅ ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ኪሞትና 26 ሕልቃና፤ የሕልቃና ወንዶች ልጆች፤
ልጁ ሱፊ፣
ልጁ ናሐት፣
27ልጁ ኤልያብ፣
ልጁ ይሮሐም፣ ልጁ ሕልቃና፣
ልጁ ሳሙኤል
አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች (እንዲሁም 1ሳሙ 1፥1920 እና 1ዜና 6፥3334 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ልጁ ሳሙኤል የሚለውን ሐረግ አይጨምርም

28የሳሙኤል ወንዶች ልጆች፤
የበኵር ልጁ ኢዮኤል
አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞችና ሱርስቱ (እንዲሁም 1ሳሙ 8፥2 እና 1ዜና 6፥33 ይመ) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ኢዩኤል የሚለውን ስም አይጨምርም።

ሁለተኛው ልጁ አብያ።
29የሜራሪ ዘሮች፤
ሞሖሊ፣ ልጁ ሎቤኒ፣
ልጁ ሰሜኢ፣ ልጁ ዖዛ፣
30ልጁ ሳምዓ፣ ልጁ ሐግያ፣
ልጁ ዓሣያ።

የቤተ መቅደሱ መዘምራን

6፥54-80 ተጓ ምብ – ኢያ 21፥4-39 31ታቦቱ ከገባ በኋላ፣ ዳዊት የመዘምራን አለቃ አድርጎ በእግዚአብሔር ቤት የሾማቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ 32እነርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣ በማደሪያው፣ ይኸውም በመገናኛው ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፤ አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው።

33ከወንዶች ልጆቻቸው ጋር ሆነው ያገለገሉ ሰዎች እነዚህ ናቸው፤

ከቀዓታውያን ልጆች፤ ዘማሪው ኤማን፣ የኢዮኤል ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ፣
34የሕልቃና ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ፣
የኤሊኤል ልጅ፣ የቶዋ ልጅ፣
35የሱፍ ልጅ፣ የሕልቃና ልጅ፣
የመሐት ልጅ፣ የአማሢ ልጅ፣
36የሕልቃና ልጅ፣ የኢዮኤል ልጅ፣
የዓዛርያስ ልጅ፣ የሶፎንያስ ልጅ፣
37የታሐት ልጅ፣ የአሴር ልጅ፣
የአብያሳፍ ልጅ፣ የቆሬ ልጅ፣
38የይስዓር ልጅ፣ የቀዓት ልጅ፣
የሌዊ ልጅ፣ የእስራኤል ልጅ።
39እንዲሁም የሔማን ወንድም አሳፍ በስተ ቀኙ ሆኖ ያገለግል ነበር፤
አሳፍ የበራክያ ልጅ፣ የሳምዓ ልጅ፣
40የሚካኤል ልጅ፣ የበዓሤያ ልጅ፣
የመልክያ ልጅ፣
41የኤትኒ ልጅ፣
የዛራ ልጅ፣ የዓዳያ ልጅ፣
42የኤታን ልጅ፣ የዛማት ልጅ፣
የሰሜኢ ልጅ፣
43የኢኤት ልጅ፣
የጌድሶን ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፤
44በስተ ግራቸው በኩል አብረዋቸው ያሉት የሜራሪ ልጆች፤
የቂሳ ልጅ ኤታን፣ የአብዲ ልጅ፣
የማሎክ ልጅ፣
45የሐሸብያ ልጅ፣
የአሜስያስ ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ፣
46የአማሲ ልጅ፣ የባኒ ልጅ፣
የሴሜር ልጅ፣
47የሞሖሊ ልጅ፣
የሙሲ ልጅ የሜራሪ ልጅ፣
የሌዊ ልጅ።

48ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ግን የእግዚአብሔርን ቤት የማደሪያ ድንኳን ተግባር እንዲያከናውኑ ተመድበው ነበር። 49የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ባዘዘው መሠረት፣ ስለ እስራኤል ማስተስረያ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የሚከናወነውን ተግባር ሁሉ፣ በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል መሥዋዕትና በዕጣኑ መሠዊያ ላይ የሚቀርበውን መሥዋዕት የሚያቀርቡት ግን አሮንና ዘሮቹ ብቻ ነበሩ።

50የአሮን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤
ልጁ አልዓዛር፣ ልጁ ፊንሐስ፣
ልጁ አቢሱ
51ልጁ ቡቂ፣
ልጁ ኦዚ፣ ልጁ ዘራእያ፣
52ልጁ መራዮት፣ ልጁ አማርያ፣
ልጁ አኪጦብ፣
53ልጁ ሳዶቅ፣
ልጁ አኪማአስ።

54መኖሪያዎቻቸው እንዲሆኑ የተመደቡላቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፦ የመጀመሪያው ዕጣ የእነርሱ ስለሆነ፣ ከቀዓት ጐሣ ለሆኑት ለአሮን ዘሮች የተመደቡላቸው መኖሪያዎች እነዚህ ነበሩ።
55ለእነርሱም በይሁዳ ምድር የምትገኘው ኬብሮንና በዙሪያዋ ያለው የግጦሽ ቦታ ተሰጠ፤ 56በኬብሮን ዙሪያ የሚገኙት የዕርሻ ቦታዎችና መንደሮች ግን ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ተሰጡ። 57ለአሮን ዘሮች የመማፀኛ ከተሞች የሆኑትን ኬብሮንን፣ ልብናን፣ የቲርን፣ ኤሽትሞዓን፣ 58ሖሎንን፣ ዳቤርን፣ 59ዓሳንን፣ ዮታን
የሱርስቱ ቅጅ (እንዲሁም የሰብዓ ሊቃናትና ኢያ 21፥16) ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ዮታን የሚለውን ስም አይጨምርም።
፣ ቤትሳሚስን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጡ።
60ከብንያም ነገድ ድርሻ ላይ ገባዖንን፣
ኢያ 21፥17 ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ዕብራይስጡ ግን ገባዖን የሚለውን ስም አይጨምርም።
ጌባን፣ ጋሌማን፣ ዓናቶትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጡ።
ለቀዓት ዘሮች የተከፋፈሉት እነዚህ ከተሞች በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ናቸው።

61ለቀሩት የቀዓት ዘሮች ደግሞ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ዐሥር ከተሞች ተሰጧቸው።
62ለጌድሶን ነገድ በየጐሣቸው ከይሳኮር፣ ከአሴር፣ ከንፍታሌምና በባሳን ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ ድርሻ ላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡላቸው።
63ለሜራሪ ዘሮች በየጐሣቸው ከሮቤል፣ ከጋድና ከዛብሎን ድርሻ ላይ ዐሥራ ሁለት ከተሞች ተመደቡላቸው።

64እስራኤላውያንም ከተሞቹን በዚሁ ሁኔታ መድበው ከነመሰማሪያዎቻቸው ለሌዋውያኑ ሰጧቸው።

65ቀደም ብለው የተጠቀሱትንም ከተሞች ከይሁዳ፣ ከስምዖንና ከብንያም ነገድ ላይ ወስደው መደቡላቸው።

66ለአንዳንድ የቀዓት ጐሣዎችም ከኤፍሬም ነገድ ድርሻ ላይ የሚኖሩበት ቦታ ተሰጣቸው።
67በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር የሚገኙትን የመማፀኛ ከተሞች ሴኬምን፣ ጌዝርን፣ 68ዮቅምዓምን፣ ቤትሖሮን፣ 69ኤሎንንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጧቸው።
70እንዲሁም እስራኤላውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ላይ ዓኔርና ቢልዓም የተባሉትን ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው ወስደው ለቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ሰጧቸው።

71ጌድሶናውያን ከዚህ የሚከተሉትን ከተሞች ወሰዱ፤
ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ በባሳን የሚገኘውን ጎላንና አስታሮትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
72ከይሳኮርም ነገድ፣ ቃዴስን፣ ዳብራትን 73ራሞትንና ዓኔምናን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
74ከአሴር ነገድ መዓሳልን፣ ዓብዶን፣ 75ሑቆቅንና፣ ረአብን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
76ከንፍታሌም ነገድ በገሊላ የሚገኘውን ቃዴስን፣ ሐሞንንና፣ ቂርያታይምን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።

77ከሌዋውያን የቀሩት የሜራሪ ጐሣዎች ደግሞ ከዚህ የሚከተለውን ወሰዱ፤
ከዛብሎን ነገድ ዮቅኒዓምን፣ ቀርታህን፣
የሰብዓ ሊቃናት ትርጕምንና ኢያ 21፥34 ይመ፤ ዕብራይስጡ ግን፣ ዮቅኒዓምን፣ ቀርታህን የሚለውን አይጨምርም።
ሬሞንና፣ ታቦርን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።
78ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ ከሚገኘው ከሮቤል ነገድ፣
በምድረ በዳ የሚገኘውን ቦሶርን፣ ያሳን፣
79ቅዴሞትንና ሜፍዓትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
80ከጋድ ነገድ በገለዓድ የምትገኘውን ሬማትን፣ መሃናይምን፣ 81ሐሴቦንና ኢያዜርን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።
Copyright information for AmhNASV